“ሮማ ካቶሊክ የእስልምና እምነት መስራች መሆንዋ ይፋ ሆነ”

“ሮማ ካቶሊክ የእስልምና እምነት መስራች መሆንዋ ይፋ ሆነ”

chrislam

በቢንያም መንገሻ june 6, 2014

በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በኢስላም የጸሎት ሰው ቁራንን በቫቲካን በሚገኘው የካቶሊክ ካቴድራል በባሳለፍነው ሳምንት እሁድ ተነበበ::  ይህንንም እንቅስቃሴ በአስተባባሪነት የመሩት የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ በፍራንሲስ አስተናጋጅነት ሲሆን የዚህም ዝግጅት ዋና አላማ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል ሰላምን ማምጣት ነው ይለናል ሚድል ኢስት የተባለው የዜና አውታር:: በትላንትናው ከሰአት ዘገባው  የዜና አውታሩ አንዳስታወቀው  የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ ፍራንሲስ እንዳስታወቁት በእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ሺሞን ፔሬዝና በፍልስጤማውያኑ አቻቸው መሀመድ አባስ ባደረጉላቸው ግብዣ ባለፈው ሳምንት ወደ ዮርዳኖስ  እስራኤልና ፍልስጤም በይፋ ያቀኑ ሲሆን ከፍልስጤም ባለስልጣናትም ጋር ተነጋግረዋል:: በማስከተልም የ ሺሞን ቃል አቀባይ ለ Times of Israel በሰጠው መግለጫ አባስ ሺሞንና ጳጳስ ፍራንሲስ ከአይሁድ ከክርስቲያንና ከእስልምና የሀይማኖት መሪዎች ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል:: በአርቡ ማታ የሁሉም ቅዱስ ጸሎት የተባለው በእስራኤላና በፍልስጤማውያን ዘንድ ግጭትን የሚያስቆምና ሰላምን ያመጣል የተባለለትን ጸሎት አድርገዋል:: ነገር ግን በአሁኑ ሰአት እስራኤልና የፍልስጤም ውዝግብ ከሚገባው በላይ ከፍታውን ጨምሮታል ይለናል አሶሼትድ ፕሬስ ይህንን ታሪካዊ ስነ ስርአት ከቫቲካን በቀጥታ ለአለም የዜናው ፕሮግራሙ በቀጥታ ሲሰራጭ እንደነበር አሶሼትድ ፕሬስ አስታውቆዋል:: ይህ በሰላም ዙሪያ የነበረው የጳጳስ ፍራንሲስ ጉብኝት ሮማ ካቶሊክ በእዚያ በኢየሩሳሌም ቅዱስ ስፍራ የባለቤትነት ይዞታ ጥያቄም ጭምር ነው ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች:: “ሰላም አንድ ሰኞ በድንገት ሰብሮ ይወጣል አሊያም ያ ሰላም ሁሉንም ይገልጣል” የጳጳስ ፍራንሲስ ንግግር አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው:: አንድ አርብ ጳጳስ ፍራንሲስ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ ጋር ተገናኝተው በኢስያ ዘላቂ የሰላም መንገድ  ለማምጣት ተወያዩ ቫቲካንም ሀሳቧ ይህ ነው ብላ አሳውቃለች ይላሉ ጳጳስ ፍራንሲስ ::

“እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።” ራእ 17:14

እኔም ይህንን ዜና እንደደረሰኝ በጣም ደነቀኝና ይበልጥ ስለ ሮማ ካቶሊክና ስለ ኢስላም ለማወቅ ፈለግኩኝ ከዛም በእዚህ እኔ ባስደነቀኝ ነገር ስለተጻፉትና ስለተሰሩት ዶክመንተሪዎችን ሳጠና የፕሮፌሰር ዋልተር ጄ. ቪዝ The Islamic Connection በሚል ያቀረቡትን ትምሀርት ቀልቤን ሳበው እሳቸው ሮማ ካቶሊክ ከኢስላም ጋር ያለቸውን ግንኙነት በማስረጃ በማስደገፍ አቀርበውታል እኔም ከቀረቡት ሀሳቦች ለዛሬ ከላይ ከቀረበው ዜና ጋር ዋና ዋና ፍሬ ሀሳቡን ለእናንተ ለወገኖቼ እንሆኝ እላለሁ:: ሙሉውን የፕሮፌሰሩን ጥናታዊ ሀሳብ ከነማስረጃው የያዘውን ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ::

  1. ካቶሊስዝም በሰይጣን ቀለበት ውስጥ ያለ የሉሲፈርያን ( የሰይጣኒዝም) ቤተ አምልኮ ነው::
  2. ሀይማኖታዊ መንፈሳዊ ጉዞ ( Pilgrimage ) እንደ  “ንግሰ ማርያም” እና “መካ” ያሉትን ጉዞዎችና አምልኮዎች ባለቤቶቹ ካቶሊኮች ሲሆኑ ይህንን የአምልኮ ስርአት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም በዋናነት ታራምደዋለች ::
  3. የኢስላም እምነት ፈጣሪ የነቢዩ መሀመድ የመጀመሪያ ሚስት ከድጃ የሮማ ካቶሊክ መነኩሴ ነበረች::
  4. በሮማ ከቶሊክ ማርያም የምትመለከውና መገለጧ የመጣው በዋሻ ውስጥ ሲሆን በኢስላም በተመሳሳይ ነብዩ መሀመድ መገለጥ የመጣለት በዋሻ ውስጥ ነው በእኛም አገር በኦርቶዶክስ እምነት ብዙ ግዜ መገለጦች ከዋሻ ውስጥ ታዩ የሚባል ዜና የተለመደ ነው አንዳንዶች የዋሻ (ገዳም) መገለጥን ለማየት ኑሮዋቸውን በዋሻ ውስጥ ካደረጉ ብዙ ዘመን ያሳለፉ ምእመና ዋሻው ይቁጠራቸው::
  5. በአለም ላይ ከሉ የእምነት መጽሀፎች “ቁራን” ልዩ ነው:: ቁራንን ልዩ የሚያደርገው በአንድ ሰው ሀሳብ ቃል በቃል ስለተጻፈ ነው የተጻፈውም በየትኛውም ቋንቋ ሳይሆን በአረቢኛ ብቻ ስለሆነ ነው::
  6. እንደ ኢንሳይክሎፒዲያ ስለሀይማኖት ዘገባ “ አላህ ” የመጀመሪያ የኢስላም ስም ሲሆን ስያሜውን ያገኘው ከባቢሎናውያን “ቤል” ነው ይለናል::
  7. “አላህ” እሱ የጨረቃ አምላክ ነው:: ከጸሀይ አምላክ ጋር ተጋብቶ አንድ ላይ በመሆን ሶስት የአማልክ ወልደዋል:: እነዚህ ሶስቱ አማልክት ባንድ ላይ ሲጠሩ አላህ ይባላሉ:: እነዚያ ሶስት አማልክት አል-ላት : አል-ዩዛ እና ማናት ይባላሉ:: ለዚህም ነው የማጭድ ቅርጽ ያለውን ጨረቃ እና ኮከብ የሚጠቀሙት በተጨማሪ በአለም ለይ ባሉት የካቶሊክ ካቴድራሎች ውስጥም ይሔንን ምልክት ይጠቀማሉ ብዙ አገሮችም የካቶሊክ ቤተ እምነትና የኢስላም መስኪድ ጎን ለጎን ሆነው ተሰርተዋል በተለይ በኢስላም አገራት ::
  8. ሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የእስልምና ሀይማኖት ብቸኛ ፈጣሪ ናት:: ይህም ከሀረቦች ጀርባ በመሆን እስራኤልን ለመቆጣጠር ነው ዋና አለማው ነው ይለናል እንዲሁም እስልምና ሀይማኖት የተፈጠረው ከካቶሊዝም ቡሀላ ነው ይለናል  የፕሮፌሰሩ መረጃ
  9. ወንጌል መስበክ በኢስላም ሀገራት በህግ አይፈቀድም::
  10. ቫቲካን የአለም የባአድ አምልኮ ስፍራ ነች::
  11. ካቶሊዝም ክርስቲያን እምነት አይደለም የሰይጣን እንጂ::
  12. የሮማ ካቶሊክ አለባበስና የኢስላም አለባበስ እና ለአምልኮ የሚጠቀሙበት መቁጠሪያ አንድ ነው እዚህ ላይ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተጨማሪ ይህንን መቁጠሪያ በመጠቀም ትታወቃለች::
  13. በኢስላም ሁሉን የማየት የአይን ምልክት የሚጠቈሙ ሲሆን ይህ የአይን ምልክት ከግብጽ ፍርኦን ሁሉን ማየት በሚለው የሉሲፈራውያን ኢልሙናቲ የሚስጥር መህበር ልዩ ምልክት ነው:: ይህ ምልክት በኢስላም አገሮች ሁሉም ይጠቀሙበታል:: በኢስላም አገሮች ይህ የአይን ምልክት በተለይ በታክሲ ስራ ላይ የጥበቃ አይን በመባል በደንብ ይታወቃል ይህ የአይን ምልክት በደንብ በአሜርካን የአንድ ዶላር ኖት ላይ በጉልህ ይታያል ይህ ምልክት በሮማ ካቶሊክ ካቴድራልና የጳጳሱ ቢሮ ህንጻ ላይ ይገኛል:: (በአለምላይ ስለዚህ ምልክትና ስለሌሎች የሰይጣን ማመለክያ ምልክቶችና ሚስጢራዊ የጣት ሰላምታዎች  ያሉትን ከእነትርጉማቸው “ስውሩ እጅ በተባለው ስለ ኢልሙናቲ 666” በተከታታይ በማወጣቸው ጽሁፎች ውስጥ ይከታተሉ::
  14. የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ዋና አላማዋ ትክክለኛውን ክርስትና እምነት እንዳይስፋፋ ማድረግ ነው::
  15. የሮማ ካቶሊክ ባለችበት ኢስላም አለ ያ ማለት ምንድ ነው ኢስልምናን በአለም ላይ ያስፋፉት ካቶሊኮች ናቸው ሉሲፈሪያን ስለሆኑ በአለም ላይ በአስደንጋጭ መልኩ በካቶሊክ አማካኝነት እስልምና ተንሰራፍቷል ይሉናል ፕሮፌሰሩ::
  16. ካቶሊክ ማንኛውም የኢስላም አገር የእራሳቸውን ቤተ አምልኮ መመስረት ሲችሉ ወንጌላዊያን ግን አይችሉም::
  17. የሚስጥራዊው ማህበር “ኢልሙናቲ 666” የመጨረሻው የማእረግ ደረጃ ላይ ሲገኙ በአላህ ያምናሉ ያመልካሉ::
  18. ሮማ ካቶሊክ የሚያመልካትና የሚያስመልካት ማርያም በራእይ መጽሐፍ ላይ ያለችው የባብሎን ንግስት ስትሆን ኢስላምም ሆነ ኦርቶዶክስ ትልቅ አምልኮ ቦታ ሰጥዋታል::
  19. ሮማ ከቶሊክ ማርያም አምላክ ነች::
  20. ሮማ ከቶሊክና ሌሎችም የሚያመልኳት ማርያም ዲያብሎስ ነች::
  21. ማርያም ብዙ ግዜ በግብጽ ታየች የሙስሊሟ ንግስትና የባቢሎን ንግስት ::
  22. “ማርያም ከሌለች ኢየሱስ የለም” ማዘር ትሬዛ
  23. ካቶሊክና ኦርቶዶክስ በመጨረሻ ኢስላም ይባላሉ:: የመጨረሻው አንድ ሀይማኖት “ክሪስኢስላም” ይባላል ክሪስኢስላም ሴጣኒዝም ሲሆን ጥምር የሚሆኑት ካቶሊክ : ኢስላምና ኦርቶዶክስ ናቸው ::
  24. አሁን በአለም ላይ ጥቅም ላይ የዋለውን ቁራን በተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ መለኪያ ያምዋላ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ይንን ቁራን ለስራው ይጠቀምበታል:: የኢስላም መልእክት ቁራን ፍጹም ትክክልና እውነት በተግባር የተደገፈ እኩልነት: ነጻነትና ወንድማማችነት የተረጋገጠበት ነው ኢስላም:: በተጨማሪ ኢስላም በውስጡ መሰረታዊ አንድነት በሁሉም ሀይማኖት ውስጥ መጀመሪ ነው ይለናል :: የተባበሩት መንግስታት በቅርቡ አዲስ የሚመሰረተው የአለም መንግስት “ “ኢልሙናቲ 666” ዋና ቢሮ ነው”
  25. በሮማ ካቶሊክ ፈጣሪነት በማርያም መረብ በቢሊዬን የሚቆጠር የአለማችን ህዝብ በሉሲፈር ቀንበር ስር ይገኛል ማርያም ባሁኑ ግዜ የቢሊዮኖችን አትኩሮት ስባለች ተኩላዎቹ የሉሲፈር ልጆች ደህንነት የሚገኘው በባቢሎኗ ንግስት በማርያም ነው ይላሉ ::

ውድ አንባቢዮቼ እነዚህንና የመሳሰሉትና ሌሎች በፕሮፌሰሩ ጥናት የቀረቡ ሲሆን የቀረበው ጥናታዊ ትምህርት ደግሞ በቪዲዮ ማስረጃ የተደገፈ መሆኑ ደግሞ ሀሳቡን አሳማኝ አድርጎታል:: እኔም ከዚህ ጥናትና ዜና በመነሳት አንድ ሁለት ነገር ለማለት ወደድኩ በአለም ባለው የስነ ህዝብ መረጃ አሀዝ መሰረት የሙስሊም ቁጥር ባለማችን ከለው ህዝብ ወደ ግማሽ እየተጠጋ ሲሆን በሀገራችንም እንደሚያሳየው መረጃ 42 ሚሊየን ሙስሊም ይገኛሉ ይህ ማለት በተለይ ኢትዮጵያ የክርስቲያን አገር ነች የሚባለውን ዲስኩር አፍ የሚያዘጋ ዜና መሆኑን ልብ ሊባል ይገባል:: ስለዚህ በደንብ አንብቦ ለተረዳው የሚያስገርመው የሙስሊሙ ቁጥር ስለበዛ ሳይሆን ክርስቲያን የሚባለው መስፈርቱ ምን እንደሆነ አለመታወቁ ነው:: ምክንያቱም አንድ አገር የክርስትያን አገር ነች ከተባለ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳ ክርስቲያን አገር ለመባል በአገሪቱ ውስጥ ካለው ነዋሪ ከ70% በላይ በክርስቶስ ኢየሱስ የዳግም ውልደት ክርስትና ያገኙ መሆን አለባቸው:: ነገር ግን አሁን ባለው የአሀዝ መረጃ የኢስላም ቁጥሩ ወደ 50% እየተጠጋ ነው:: ስለዚህ መባል ያለበት ኢትዮጵያ የሙስሊም አገር ነች እንጂ የክርስቲያን አይደለችም:: ምክንያቱም ክርስቲያን መባል የሚችሉት በስም ክርስትና እና አንገት ላይ መስቀል በማሰር ክርስቲያን የሆኑ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ክርስቶስን የተከተሉ ብቻ ናቸው እንደ ወንጌል  መሰረት ክርስትያን የሚባሉት:: እኔ አይደለም ይህን የምለው መጽሀፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል ሙሉውን ስለክርስትና እምነት እራሱ ጌታ ኢየሱስ በብዙ ቦታ ደጋግሞ አስተምሮታል:: ይሁን እንጂ ሌላው በዚህ በመጨረሻው የዘመን ፍጻሜ ደግሞ አንድ የአለም ሀይማኖት ተመስርቷል:: ስሙም “ክሪኢስላም” ይባላል ይህ ክሪስኢስላም እነዚህ በስም ክርስቲያን የተባሉት ከሙስሊሞችና ከሌሎች እምነቶች ጋር አንድ ላይ በመሆን የፈጠሩት ሀይማኖት ነው “ክሪኢስላም” ብዙን ግዜ በሀገራችን ኢስላም  ኦርቶዶክስ እና ካቶሊክ ወንጌልን እንዲሰበክ አይፈልጉም አይወዱምም ለምን ይሆን? እነሱም የክሪስኢስላም አባል ሆነው ይሆን? ወደፊት በሰፊው እናየዋለን:: ሌላው ማንሳት የምፈልገው ስለሮማ ኢምፓየር መንግስት ነው በራእይ መጻፍ ላይ የተገለጠችው ጋለሞታዋ ሴት ቫቲካን ስትሆን 7 ነገስታት አሁን ያሉት በአለማችን ሰባቱ ሀያላን አገር ናቸው ስምንት ነበሩ አንደኛው ሩስያ ከሰሞኑ በተፈጠረው ከይኩሬን ጋር በተያያዘ ፓለቲካዊ አለመግባባት ከአባልነት ቀንሰዋታል ስለዚህ ይህ የሚያመለክተው ወደ መጨረሻው 11ኛው ሰአት እየቀረብን እንደመጣን ልብ ሊባል ይገባል ሌላው ከዚህ ጋር ተያይዞ ትልቁ የመጨረሻው ዘመን የጌታ መምጣት ምልክታችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሉቃስ ወንጌል ምእራፍ 21 ያለውን ነገር ብናስተውል ብዙ ነገሮች በዚህች አለም ላይ ተፈጽሟል እየተፈጸመም ነው:: እንዲሁም በኢሳያስ መጽሐፍ ምእራፍ 17 እና 19 ስለ ሶሪያና ስለ ግብጽ የተጻፈውን ብታነቡ እና እነዚህ ሁለት አገሮች ያሉበትን ፓለቲካዊ ሁኔታ ብታገናዝቡ ባላችሁበት የስግደት አምልኮ ወደ እግዚያብሔር እንደምታቀርቡ እምነቴ ነው:: ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ትንቢቶች በተግባር እየታየ ስለሆነ:: ሌላው ኢየሩሳሌም በጭፍራ ተከባ ባያችኋት ግዜ ጌታ ያለን ነገር ስለ ጎግ ማጎግ ጦርነት  እንደተቃረበ በጣም በሚገርም ሁኔታ ስለዚህ ጦርነት ምልክት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቢንያሚን ናታኒሁን በእዚህ አመት ለተባበሩት መንግስታት የመሪዎች ስብሰባ ላይ በግልጽ ተናግረዋል:: የዚህን ጦርነት ሙሉውን መረጃ እነደ ጌታ ፈቃድ ከሰሞኑ ላዘጋጅና ላቀርብ እወዳለሁ ለዛሬ በእዚህ ልቋጭ እያልኩ በሚቀጥለው የብእር ማእዴ እስክንገናኝ መልካም የንባብ ግዜ ይሁንላችሁ  እላለሁ::

“ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና። እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።ገና ከእናንተ ጋር ሳለሁ፥ ይህን እንዳልኋችሁ ትዝ አይላችሁምን? በገዛ ራሱ ጊዜም ይገለጥ ዘንድ፥ የሚከለክለውን አሁን ታውቃላችሁ። የዓመፅ ምሥጢር አሁን ይሠራልና፤ ብቻ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን የሚከለክል አለ።በዚያም ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው፥ ሲመጣም በመገለጡ የሚሽረው ዓመፀኛ ይገለጣል፤ ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው። ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።”

2ኛ ተሰሎንቄ 3-12

ማራናታ !

About " ማራናታ " !

“የተወደዳችሁ ውድ የዚህ ጦማር ተቋዳሾች በእግዚያብሔር ቸርነት እና ፈቃድ በተከታታይ የማወጣቸውን ጽሁፎች እንድትመገቡልኝና እንድታጣጥሙልኝ በስተመጨረሻም ያጣጣማችሁትን ጣእም ደግሞ እንድታሳውቁኝ በእግዚያብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እጠይቃችኋለው ምክንያቱም ለመውጣትም ሆነ ለመውረድ የእናንተን ጣእም በጣም ወሳኝ ነውና ይህንን መጦመሪያ እንዳዘጋጅ የረዳኝ እግዚያብሔር ነው:: እኔ ብዙ ግዜ እንዲህ በማለት አምን ነበረ ማንኛውም ነገር በሰው ሀይል የተፈለገው ነገር ሁሉ ይገኛል የሚል የጸና እምነት ነበረኝ ለዚህም በፓለቲካዊና በማነቸውም ለለውጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ የአቅሜንና ያመንኩበትን ሀሳብ ተሳትፎና ድጋፍ አደርግ ነበረ ነገር ግን ይህ የሚፈለገው ፓለቲካም ሆነ ማንኛውም ለውጥ ግን ከዛሬ ነገ ይሻላል ሲባል የሚፈገለገው ነገር ከመባሱ በስተቀር ጠብ ያለ ነገር የለም ስለዚህም ያልተኬደበትን መንገድ መፈለግ ጀመርኩ መንገዱን የጀመርኩት ከእራሴ በመነሳት ነው እራሴን ጠየቅኩኝ እኔ ማን ነኝ? ወደ እዚህች አሰቃቂ አለም እንዴት መጣሁ? እኔ ፈልጌ ነው ወይስ ቤተሰቦቼ? የት ድረስ ነው አቅሜ? ያለፉት ህይወቶቼ ምን ይመስል ነበር? ከአሁን ቡኋላ እንዴት ነው ሀይወቴን የምገፋው? ሌሎችንም ጥያቄ ይዤ በእምነቴም ክርስቲያንም ስለሆንኩ ወደ አመንኩት አምላክ ወደ እግዚያብሔር ቃል ዞርኩ ሁሉን ወደሚችለውና ወደ ሚያውቀው የእግዚያብሔርን ቃል ማጥናት ስጀምር እያንዳንዷን የዚህችን አለምና ስንክሳርና የሚመጣውን ጭምር የሚናገር መጽሀፍ ሆኖ አገኘሁት መጽሀፍ ቅዱስን በጣም ደግሞ የገረመኝ ሌላው ቢቀር አሁን ያለውን ነባራዊ የአከም ሁኔታ እንኳ ስለግብጽና ስለሶሪያ በደንብ አስረግጦ ይነግረናል:: በአለም ላይ እየተደረጉ ስላሉት ሀይማኖታዊ : ፓለቲካዊ : ኢኮኖሚያዊ : ማህበራዊ ቀውሶችን እና መፍትሄያቸውንም ጭምር ይነግረናል ይህንን ታላቅ መጻፍ ለምን ሰው ዝም ብሎ ተራራ ከሚገፋ እውነቱን አውቆ በቀላሉ ወደ እግዚያብሔር በመዞር ያን ለሰው ተራራ የሆነውን ለእግዚያብሔር ደግሞ አይኑ ወስጥ የማይገባውን ነገር ለእግዚያብሔር አስረክቦ ባሸናፊው አምላክ አያሸንፍም ብዬ አሰብኩና የገባኝን የምድራችን ስንክ ሳር በእግዚያብሔር ቃል መክፈቻ እየከፈትኩ ለወገኖቼ አላቀርብም በማለት በልቤ አሰብኩ እግዚያብሔርም እረድቶኝ ሀሳቤ እውን ሆነ በፌስ ቡክ ላይ በጅማሬ የተጀመረው ይህ ጦማር ዛሬ “ማራናታ” በሚል የመጦመሪያ ስም እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ለእናንተ የንባብ ማእድ በሩ ክፍት አድርጌ እንሆኝ እላለው:: ማሳሰብ የምፈልገው መነገር የምፈልገው የሀይማኖት ስርአት ለማስተማር አስቤ ሳይሆን የአለማችንን ጉድ በሙሉ የያዘውን የእግዚያብሔር ቃል እንድታዩት ለማሰታወስ ነው:: መልካም ማእድ ይሁንላችሁ በማለት ልባዊ እምነቴ ነው::” የእግዚያብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በነገር ሁሉ ላይ ጌታ ነው:: ! የእግዚያብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከነገር ሁሉ ያድናል:: ! ማራናታ ! አሜን ! ጌታ ሆይ ቶ ሎ ና ! ቢንያም መንገሻ
This entry was posted in News. Bookmark the permalink.

Leave a comment